እነርሱም፥ “ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ፤ ሕልማችሁ ምንድን ነው?”
መክብብ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐዋቂዎችን ማን ያውቃቸዋል? ቃላቸውንስ መተርጐም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበራለች፥ በፊቱም ኀፍረት የሌለው ሰው ይጠላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣ እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢብን የሚመስለው? የነገሮችንስ ትርጒም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱንም ድንዳኔ ትለውጣለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኛን የሚመስለው ማነው? የነገሮችን ፍቺ የሚያውቅ ማነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ ኰስታራነትንም ትለውጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጐም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱንም ድፍረት ትለውጣለች። |
እነርሱም፥ “ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ፤ ሕልማችሁ ምንድን ነው?”
የሞት መላእክት ምንም ሺህ ቢሆኑ፥ በልቡ ወደ እግዚአብሔር ሊመለስ ቢያስብ፥ ኀጢአቱን ለሰው ቢናገር፥ በደሉንም ቢገልጥ፥ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይገድለውም፤
የእስራኤልም ልጆች የሙሴን ፊት እንዳንጸባረቀ ያዩ ነበር፤ እርሱም ከእርሱ ጋር ሊነጋገር እስኪገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸፈኛ ያደርግ ነበር።
ጴጥሮስና ዮሐንስም ግልጥ አድርገው ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፥ ያልተማሩና መጽሐፍን የማያውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐውቀው አደነቁ፤ ሁልጊዜም ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።