እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
መክብብ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ሥራዬን አበዛሁ፥ ቤቶችንም ለእኔ ሠራሁ፥ ወይንም ተከልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላላቅ ነገሮችን አከናወንሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንንም ተከልሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትልቅ ሥራን ሠራሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ገነባሁ፥ ወይንንም ተከልሁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም አንድ ትልቅ ነገር ፈጸምኩ፤ ይኸውም፥ መኖሪያ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይን ተከልኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትልቅ ሥራን ሠራሁ፥ ቤቶችንም አደረግሁ፥ ወይንም ተከልሁ፥ |
እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
አቤሴሎምም በሕይወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” ብሎ ሐውልት ወስዶ በንጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤሴሎም” ተብላ ትጠራለች።
“በእኔና በአንተ መካከል በአባቴና በአባትህ መካከል ቃል ኪዳን ጸንቶአል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረከት ልኬልሃለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እንዲርቅ ሄደህ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ” ብሎ ላከ።
ከዚህም በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን ያደርገው ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥
በወይንም ቦታዎች ላይ ራማታዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወይንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚሆነው በወይኑ ሰብል ላይ የሳፍኒው ዘብዲ ሹም ነበረ።
በምድረ በዳውም ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ በቆላውና በደጋው ብዙ እንስሶች ነበሩትና፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
ሰሎሞንም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት።
አሁን የወይኔን ቦታ በተመለከተ የወዳጄን መዝሙር ለወዳጄ እዘምራለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ቦታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።