እግዚአብሔርም አዳምን አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ከአዘዝሁህ ከዚያ ዛፍም በልተሃልና ምድር በሥራህ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
መክብብ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚያም ነው፤ ልቡም በሌሊት አይተኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘመኑ ሁሉ ሥራው ሥቃይና ሐዘን ነው፤ በሌሊትም እንኳ ቢሆን አእምሮው አያርፍም። ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘመኑ ሁሉ ስቃይ፥ ጥረትም ትካዜ ነው፥ ልቡም በሌሊት አያርፍም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወቱ ዘመን የሚሠራው ነገር ሁሉ ከሐዘንና ከትካዜ በቀር የሚያተርፍለት ምንም ዐይነት ጥቅም የለም፤ ሌሊት እንኳ አእምሮው ዕረፍት አያገኝም፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘመኑ ሁሉ ኀዘን፥ ጥረትም ትካዜ ነው፥ ልቡም በሌሊት አይተኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። |
እግዚአብሔርም አዳምን አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ከአዘዝሁህ ከዚያ ዛፍም በልተሃልና ምድር በሥራህ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፥ “በእንግድነት የኖርሁት የሕይወቴ ዘመንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴም ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፤ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
ከሰማይም በታች ስለተደረገው ሁሉ በጥበብ ለመመርመርና ለመፈተን ልቤን አተጋሁ፤ እግዚአብሔር ይደክሙበት ዘንድ ክፉ ድካምን ለሰው ልጆች ሰጥትዋልና።
እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ፥ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።
ጥበብን አውቅ ዘንድ በምድር የሚሆነውንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀንና በሌሊት እንቅልፍን በዐይኑ የሚያይ የለምና።
የደቀ መዛሙርትንም ልቡና አጽናኑ፤ በሃይማኖትም እንዲጸኑ፦“ በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” እያሉ መከሩአቸው።