La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ነው፤ አንተ እን​ደ​ም​ታ​ርፍ ሎሌ​ህና ገረ​ድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ በሬ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም ሁሉ፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ በእ​ርሱ ምንም ሥራ አት​ሥሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በዚያ ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ በሬህ፣ አህያህ ወይም ማንኛውም እንስሳህ ወይም ደግሞ በደጅህ ያለ እንግዳ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩ። ይህም አንተ እንዳረፍህ ሁሉ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ እንዲያርፉ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ምንም ዐይነት ሥራ አትሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ አገልጋዮችህም ልክ እንደ አንተው ዕረፍት ያድርጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር አምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም ሎሌህም ገረድህም በሬህም አህያህም ከብትህም ሁሉ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 5:14
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሠ​ራ​ውን ሥራ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሠ​ራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።


በዚ​ያም ወራት በይ​ሁዳ በሰ​ን​በት ቀን የወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያን የሚ​ረ​ግ​ጡ​ትን፥ ነዶም የሚ​ከ​ም​ሩ​ትን፥ የወ​ይ​ኑን ጠጅና የወ​ይ​ኑን ዘለላ፤ በለ​ሱ​ንም፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸክም በአ​ህ​ዮች ላይ የሚ​ጭ​ኑ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​ትን አየሁ፤ ገበ​ያም ባደ​ረ​ጉ​በት ቀን አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸው።


ደግ​ሞም በእ​ር​ስዋ የተ​ቀ​መጡ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም ዓሣ​ዎ​ችን፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸቀጥ አም​ጥ​ተው በሰ​ን​በት ቀን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለይ​ሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር።


እኔም አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውና፥ “ከቅ​ጥሩ ውጭ ለምን ታድ​ራ​ላ​ችሁ? እንደ ገና ብታ​ደ​ር​ጉት እጆ​ችን አነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ” አል​ኋ​ቸው። ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ በሰ​ን​በት ቀን እንደ ገና አል​መ​ጡም።


አሁ​ንም ሥጋ​ችን እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሥጋ፥ ልጆ​ቻ​ች​ንም እንደ ልጆ​ቻ​ቸው ናቸው፤ እነ​ሆም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥ​ተ​ናል፤ ከሴ​ቶ​ችም ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ሆነው የሚ​ኖሩ አሉ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን ይዘ​ዋ​ልና ልና​ድ​ና​ቸው አን​ች​ልም” የሚሉ ነበሩ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሁሉ ሥራ፤ በሬ​ህና አህ​ያህ ያርፉ ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህም ልጅ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም ዕረ​ፍት ይሆን ዘንድ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዕረፍ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።


ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤


ስድ​ስት ቀን ሥራ፤ ተግ​ባ​ር​ህ​ንም ሁሉ አድ​ርግ፥


ስለ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሥ​ራው ሁሉ ዐረፈ” ብሎ​አ​ልና።