እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣኻቸው ሕዝብህ በድለዋልና ሂድ፤ ፈጥነህ ውረድ።
ዘዳግም 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳትበድሉ፥ የተቀረጸውን ምስል፥ የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ በምድር ላይ ያለውን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም እንዳትረክሱ፣ በወንድ ወይም በሴት መልክ በማንኛውም ዐይነት ምስል የተቀረጸ ጣዖት ለራሳችሁ እንዳታበጁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማናቸውንም መልክ በየትኛውም ምስል፥ በወንድ ይሁን በሴት መልክ፥ የተቀረጸውን ምስል ለራሳችሁ በማድረግ እንዳትረክሱ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በወንድ ወይም በሴት መልክ ቅርጽ በመሥራት እንዳትረክሱ ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ |
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣኻቸው ሕዝብህ በድለዋልና ሂድ፤ ፈጥነህ ውረድ።
ጠራቢውም እንጨት ቈርጦ በልኩ ያቆመዋል፤ በማጣበቂያም ያያይዘዋል፤ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል፤ በቤትም ውስጥ ያቆመዋል።
እኔም ገባሁና፥ እነሆ በግንቡ ዙሪያ ላይ የተንቀሳቃሾች አዕዋፍና እንስሳትን ምሳሌ ከንቱና ርኩስ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተሥለው አየሁ።
ጣዖታትንም አትከተሉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የአማልክት ምስሎች ለእናንተ አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
“ለእናንተ በእጅ የተሠራ ጣዖት አታድርጉ፤ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
እንግዲህ እኛ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆን በሰው ዕውቀትና ብልሀት በተቀረጸ በድንጋይና በብር፥ በወርቅም አምላክነቱን ልንመስለው አይገባም።
“በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን፥ የተቀረፀ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።
ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንድትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ፈቀቅ እንድትሉ አውቃለሁና። በእጃችሁም ሥራ ታስቈጡት ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስላደረጋችሁ፥ በኋለኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገኛችኋል።”
ከእናንተ ጋር የተማማለውን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የከለከለውን፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ እንግዲህ ተጠንቀቁ።
“ልጆችን፥ የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ረዥም ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በበደላችሁም ጊዜ፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል ባደረጋችሁ ጊዜ፥ ታስቈጡትም ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ፥
“በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር ማንኛውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
እግዚአብሔርም አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፤ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ በድለዋልና፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋልና፥ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አድርገዋልና።