Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 32:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኻ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና ሂድ፤ ፈጥ​ነህ ውረድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ከግብጽ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ስተዋልና ውረድ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ በድለዋልና ሂድ ውረድ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ ራሱን ስላረከሰ ፈጥነህ ውረድ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:7
17 Referencias Cruzadas  

አባ​ቱም ዖዝ​ያን እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ አል​ገ​ባም፤ ሕዝ​ቡም ገና ይበ​ድል ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮ​ንም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ካህ​ና​ቱና ሕዝቡ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወጡ ዘንድ አይ​ደ​ፋ​ፈሩ” አለው።


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በጽኑ እጅ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኸው በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለምን ተቈ​ጣህ?


ከእ​ጃ​ቸ​ውም ተቀ​ብሎ በመ​ቅ​ረጫ ቀረ​ጸው፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ጥጃም አደ​ረ​ገው፤ እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ሂድ፤ አንተ ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኸው ሕዝ​ብህ ጋር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ወደ ማል​ሁ​ባት ምድር ውጣ።


ኀጢ​አ​ተኛ ወገ​ንና ዐመፅ የተ​ሞ​ላ​በት ሕዝብ፥ የክ​ፉ​ዎች ዘር፥ በደ​ለ​ኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮ​ላ​ችሁ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዋ​ች​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።


በጊ​ብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፤ እር​ሱም በደ​ላ​ቸ​ውን ያስ​ባል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይበ​ቀ​ላል።


ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”


እነ​ርሱ በደሉ፤ ልጆ​ቹም አይ​ደ​ሉም፤ ነው​ርም አለ​ባ​ቸው፤ ጠማ​ማና ገል​በ​ጥ​ባጣ ትው​ልድ ናቸው።


እን​ዳ​ት​በ​ድሉ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል፥ የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ምሳሌ፥ በወ​ንድ ወይም በሴት መልክ የተ​ሠ​ራ​ውን፥ በም​ድር ላይ ያለ​ውን፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ ፈጥ​ነው ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና፥ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም ለራ​ሳ​ቸው አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።


በኮ​ሬብ ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ና​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ በእ​ና​ንተ ላይ ተቈጣ።


መስ​ፍኑ ግን ከሞተ በኋላ ዳግ​መኛ ተመ​ል​ሰው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ይልቅ እጅግ ይበ​ድሉ፤ ነበር፤ ሂደ​ውም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው ያመ​ል​ኳ​ቸው ነበር፤ ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አይ​መ​ለ​ሱም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos