እንዲህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፤ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፤ በሰገነቱም ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ የተዋበች መልከ መልካም ነበረች።
ዘዳግም 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አዲስ ቤት በሠራህ ጊዜ ማንም ከእርሱ ወድቆ በቤትህ ግድያ እንዳታደርግ ለሰገነትህ መከታ አድርግለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፣ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፣ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ በጣራው ክፈፍ ዙሪያ መከታ አድርግለት፤ አለበለዚያ አንድ ሰው ከጣራው ላይ ቢወድቅ ለደሙ ተጠያቂ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዲስ ቤት በሠራህ ጊዜ ማንም ከእርሱ ወድቆ ደሙን በቤትህ ላይ እንዳታመጣ በጣራው ዙሪያ መከታ አድርግለት። |
እንዲህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፤ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፤ በሰገነቱም ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ የተዋበች መልከ መልካም ነበረች።
“እሳት ቢነሣ ጫካውንም ቢይዝ፥ ዐውድማውንም፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል እሳቱን ያነደደው ይክፈል።
የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ፤ እነዚያም በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ።”
እኔ ኀጢአተኛውን፥ “በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ አንተም ባትነግረው፥ ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኀጢአተኛው ባትነግረው፥ ያ ኀጢአተኛ በኀጢአቱ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕንቅፋት ባደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አልነገርኸውምና በኀጢአቱ ይሞታል፤ ያደረጋትም የጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንነቃቀፍ፤ ይልቁንም ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖር ይህን ዐስቡ።
“ፍሬውንና የዘራኸውን ዘር ከወይንህ ፍሬ ጋር እንዳትለቅም በወይንህ ቦታ ላይ የተለያየ ዓይነት ተክል አትትከል።
የሚሻለውን ሥራ እንድትመረምሩና እንድትፈትኑ፥ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ያለ ዕንቅፋት ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፦