አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።
ዘዳግም 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመንገድ በማናቸውም ዛፍ ላይ ወይም በመሬት ላይ ከጫጭቶችና ከእንቍላል ጋር እናቲቱ በእነዚህ ላይ ተቀምጣ የወፍ ጎጆ ብታገኝ እናቲቱን ከጫጭቶችዋ ጋር አትውሰድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ ስታልፍ፣ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቍላሎቿን የታቀፈችበትን ጐጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኝ፣ እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በመንገድ ስትሄድ አንዲት ወፍ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ጫጩቶችዋንም ሆነ እንቁላሎችዋን ዐቅፋ የተቀመጠችበትን ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ወፍ ከነጫጩቶችዋ አትውሰድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንዲት ወፍ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ጫጩቶችዋንም ሆነ እንቊላሎችዋን ዐቅፋ የተቀመጠችበትን ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ወፍ ከነጫጩቶችዋ አትውሰድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንገድ ስትሄድ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ እናቲቱ በጫጩቶችዋ ወይም በእንቁላሎችዋ ላይ ተኝታ ሳለች የወፍ ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ከጫጩቶዋ ጋር አትውሰድ። |
አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።
ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ከአንተ ጋር አውጣቸው፤ በምድርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድርንም ሙሉአት።”
በሕዝብህም መካከል ጥፋት ይነሣል፤ እናትም በልጆችዋ ላይ በተጣለች ጊዜ የሰልማን አለቃ ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።
“ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።