“ተሳዳቢውን ከሰፈር ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት።”
ዘዳግም 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፣ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ ክፉን ከመካከልህ አስወግድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፥ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምስክሮቹ የመጀመሪያዎቹን ድንጋዮች ይወርውሩ፤ ከዚያም ቀጥሎ ሌላው ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው፤ በዚህም ዐይነት እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ሁሉ ከመካከልህ ታስወግዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ። |
“ተሳዳቢውን ከሰፈር ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት።”
ብዙ ጊዜ መላልሰው በጠየቁት ጊዜም ዐይኖቹን አንሥቶ፥ “ከእናንተ ኀጢኣት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት” አላቸው።
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና በድንጋይ ይውገሩት፤ ይግደሉትም።
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በአምላክህ እግዚአብሔር ስም ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም በዚያ ወራት ያለውን ፈራጁን ባይሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእስራኤልም ዘንድ ክፉውን አስወግዱ፤
በወንድሙ ላይ ክፋትን ያደርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእርሱ ላይ ታደርጉበታላችሁ፤ እንዲሁም ከእናንተ መካከል ክፉውን ታስወግዳላችሁ።
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ሁለታቸው ይገደሉ፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከእስራኤል ታስወግዳለህ።
ብላቴናዪቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውየውም የባልጀራውን ሚስት አስነውሮአልና በድንጋይ ወግረው ይግደሉአቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ።
“ማንም ሰው ከእስራኤል ልጆች ከወንድሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰርቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰረቀውን ሰው ይግደሉት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አርቁ።
“አሁንም በገባዖን ውስጥ የበደሉ የዐመፅ ሰዎችን እንድንገድላቸው አውጥታችሁ ስጡን፤ ከእስራኤልም ልጆች ክፋትን እናርቃለን።” የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም።