Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 22:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ብላ​ቴ​ና​ዪቱ በከ​ተማ ውስጥ ሳለች አል​ጮ​ኸ​ች​ምና፥ ሰው​የ​ውም የባ​ል​ጀ​ራ​ውን ሚስት አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ነገር ከው​ስ​ጥህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፣ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስገድዶ ስለ ደፈረ፣ ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፥ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዬውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፥ በዚህም ዓይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 22:24
14 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “እን​ግ​ዲህ ወደ እር​ስዋ እገባ ዘንድ ሚስ​ቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈ​ጽ​ሞ​አ​ልና አለው።”


የሌ​ላ​ውን ወንድ ሚስት ማር​ከስ፥ የማ​ይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩት የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት ነው።


በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ችና በደም አፍ​ሳ​ሾች በቀል እበ​ቀ​ል​ሻ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትና በቅ​ን​አት ደምም አስ​ቀ​ም​ጥ​ሻ​ለሁ።


“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ቢያ​መ​ነ​ዝር አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ።


እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።


ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤


በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።


እና​ን​ተም ከዚህ ጋር ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ናችሁ፤ ይል​ቁ​ንም ይህን ያደ​ረ​ገው ከእ​ና​ንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላ​ዘ​ና​ች​ሁ​በ​ትም?


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በመ​ጀ​መ​ሪያ የም​ስ​ክ​ሮች እጅ በኋ​ላም የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ ትሁ​ን​በት፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ።


ከዚ​ያም በኋላ በእ​ር​ስዋ ደስ ባይ​ልህ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ትለ​ቅ​ቃ​ታ​ለህ፤ በዋጋ ግን አት​ሸ​ጣ​ትም፤ አግ​ብ​ተ​ሃ​ታ​ልና እን​ደ​ባ​ሪያ አት​ቍ​ጠ​ራት።


“ለወ​ንድ የታ​ጨች ድን​ግል ልጅ ብት​ኖር፥ ሌላ ሰውም በከ​ተማ ውስጥ አግ​ኝቶ ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለ​ቱን ወደ​ዚ​ያች ከተማ በር አው​ጡ​አ​ቸው፤


“ነገር ግን ሰው የታ​ጨ​ች​ውን ልጃ​ገ​ረድ በሜዳ ቢያ​ገ​ኛት፥ በግድ አሸ​ን​ፎም ቢደ​ር​ስ​ባት፥ ያ የደ​ረ​ሰ​ባት ሰው ብቻ​ውን ይገ​ደል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos