እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችን ሠሩ፤ ሐውልቶችንና የማምለኪያ አፀዶችንም ለራሳቸው አቆሙ።
ዘዳግም 16:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም የሚጠላውን የማምለኪያ ሐውልት ለአንተ አታቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠላውን የማምለኪያ የድንጋይ ምሰሶ አታቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም። |
እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችን ሠሩ፤ ሐውልቶችንና የማምለኪያ አፀዶችንም ለራሳቸው አቆሙ።
“በላይ በሰማይ ከአለው፥ በታችም በምድር ከአለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ከአለው ነገር የማናቸውንም ምስል ለአንተ አምላክ አታድርግ።
ነገር ግን መሠውያዎቻቸውን ታፈርሳላችሁ፤ ሐውልቶቻቸውንም ትሰብራላችሁ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውን ትቈርጣላችሁ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት ታቃጥላላችሁ፤
“ለእናንተ በእጅ የተሠራ ጣዖት አታድርጉ፤ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፣ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፣ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአምላኮቻቸው በእሳት ስለሚያቃጥሉ አሕዛብ ለአምላኮቻቸው የሚያደርጉትን ርኩስ ነገር እግዚአብሔር ይጠላልና።
እንዳትበድሉ፥ የተቀረጸውን ምስል፥ የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ በምድር ላይ ያለውን፥
ከእናንተ ጋር የተማማለውን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የከለከለውን፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ እንግዲህ ተጠንቀቁ።
“ልጆችን፥ የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ረዥም ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በበደላችሁም ጊዜ፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል ባደረጋችሁ ጊዜ፥ ታስቈጡትም ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ፥