Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በረ​ጃ​ጅሙ ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ ዐም​ዶ​ችን ተከሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በእያንዳንዱ ኰረብታ ላይና በእያንዳንዱም የተንሰራፋ ዛፍ ሥር ዐምደ ጣዖትና የአሼራን ምስል ዐምዶች አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በኰረብቶች ሁሉ ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር የድንጋይ ዐምዶችንና አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎች አቆሙ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በኰረብቶች ሁሉ ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር የድንጋይ ዐምዶችንና አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎች አቆሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በረጃጅሙ ኮረብታ ሁሉ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ ታች ሐውልቶችንና የማምለኪያ ዐፀዶችን ተከሉ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 17:10
14 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠ​ሉም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ች​ንም ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ።


የማምለኪያ ዐፀዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፥ ከተሞችህንም አፈርሳለሁ።


በመ​ስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


ነገር ግን መሠ​ው​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ብ​ራ​ላ​ችሁ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ውን ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ፤


እና​ንተ በለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣ​ዖት ደስ የም​ት​ሰኙ፥ እና​ን​ተም በሸ​ለ​ቆች ውስጥ በዓ​ለ​ትም ስን​ጣ​ቂ​ዎች በታች ልጆ​ቻ​ች​ሁን የም​ት​ሠዉ፥ እና​ንተ የጥ​ፋት ልጆ​ችና የዐ​መ​ፀ​ኞች ዘሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?


“ለአ​ንተ በም​ት​ሠ​ራው በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ከማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ አድ​ር​ገህ አት​ት​ከል።


“ለእ​ና​ንተ በእጅ የተ​ሠራ ጣዖት አታ​ድ​ርጉ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸም ምስል ወይም ሐው​ልት አታ​ቁሙ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም ዘንድ በም​ድ​ራ​ችሁ ላይ የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ አታ​ኑሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


በመ​ካ​ከ​ልህ ወጥ​መድ እን​ዳ​ይ​ሆ​ኑ​ብህ አንተ በም​ት​ገ​ባ​በት ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው አሕ​ዛብ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት፥ በኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንና ሐው​ል​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ጠ​ላ​ውን ሐው​ልት ለአ​ንተ አታ​ቁም።


ምድ​ራ​ቸ​ውም በእ​ጆ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በጣ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሠ​ሩ​አ​ቸው ይሰ​ግ​ዳሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን እን​ዲህ አለኝ፥ “ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን አየ​ህን? ወደ ረዘ​መው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመ​ለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚ​ያም አመ​ነ​ዘ​ረች።


እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios