ዘዳግም 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፤ ከተማይቱንም፥ ዕቃዋንም ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘለዓለምም ወና ትሆናለች፤ ደግሞም አትሠራም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፥ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ ለጌታ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘለዓለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚያችን ከተማ ሰዎች ሀብት በሙሉ ሰብስበህ በማምጣት በከተማይቱ አደባባይ እንዲከመር አድርግ፤ ከዚያም በኋላ ከተማይቱንና ሀብቱን ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ በእሳት አቃጥለው፤ ዳግመኛም እንዳትሠራ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆና ትቅር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘላለምም ወና ትሆናለች፥ ደግሞም አትሠራም። |
ከተሞችን ትቢያ አደረግህ፤ የተመሸጉ ከተሞችን፥ የኃጥኣንንም መሠረት አፈረስህ፤ ከተሞቻቸውም ለዘለዓለም አይሠሩም።
ስለዚህ እነሆ በአሞን ልጆች ከተማ በራባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለጥፋትም ትሆናለች፥ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።
እንደ ተራቈተ ድንጋይ አደርግሻለሁ፤ የመረብም ማስጫ ትሆኛለሽ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አትሠሪም፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፥ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።
የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ ከእነርሱም የተሠራባቸውን ብርንና ወርቅን፥ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትበድልበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ኢያሱም ከተማዋን፥ በከተማዪቱም ውስጥ የነበሩትን ሁሉ፥ ከወንድ እስከ ሴት፥ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።
ከተማዪቱንም፥ በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን፥ የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።
በዚያችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረቷን በበኵር ልጁ የሚጥል፥ በሮችዋንም በታናሹ ልጁ የሚያቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።
ኢያሱም ከተማዋን በእሳት አቃጠላት፤ ዐመድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘለዓለሙ የሚኖርባት እንዳይኖር አደረጋት።