La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደሙን ግን እንደ ውኃ በም​ድር ላይ አፍ​ስ​ሱት እንጂ አት​ብ​ሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ደማቸውን አትብላ፤ ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 12:16
15 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤


ደም​ዋም በመ​ካ​ከ​ልዋ አለ። በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አደ​ረ​ገ​ችው እንጂ በአ​ፈር ይከ​ደን ዘንድ በመ​ሬት ላይ አላ​ፈ​ሰ​ሰ​ች​ውም።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም ወደ ጣዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ታነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ደም​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?


“በተ​ራራ ላይ አት​ብሉ፤ አት​ር​ከሱ፥ በወ​ፍም አታ​ሟ​ርቱ።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ትበ​ላ​ዋ​ለህ፤ ንጹሕ ሰው፥ ንጹ​ሕም ያል​ሆነ፥ ሚዳ​ቋ​ንና ዋሊ​ያን እን​ደ​ሚ​በሉ ይበ​ሉ​ታል።


ነገር ግን ደሙን በም​ድር ላይ እንደ ውኃ አፍ​ስ​ሰው እንጂ አት​ብ​ላው።


እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤


ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ።


ለሳ​ኦ​ልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደሉ” ብለው ነገ​ሩት። ሳኦ​ልም በጌ​ቴም “ትልቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ አቅ​ር​ቡ​ልኝ” አላ​ቸው።