ዘዳግም 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራትን ሥርዐትና ፍርድ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ በፊታችሁ እኔ ያስቀመጥኋቸውን ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ ለመፈጸም ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ በፊታችሁ እኔ ያስቀመጥኳቸውን ሥርዓቶችና ሕጎች ሁሉ ለመፈጸም ትጉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራትን ሥርዓትና ፍርድ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ። |
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዕጣችሁ ለሁልጊዜ የሚሰጣችሁን ምድር ትገቡና ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፤ ትወርሱአታላችሁም፤ ትቀመጡባታላችሁም።
“በምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ትወርሷት ዘንድ በሚሰጣችሁ ሀገር ታደርጉት ዘንድ የምትጠብቁት ሥርዐት፥ ፍርድም ይህ ነው።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።
“ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤