አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት፥ መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ” አላቸው።
ዘዳግም 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶች ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኀያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድም የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከባዕዳን አማልክት ሁሉና ከኀይላትም ሁሉ በላይ ታላቅና ብርቱ ስለ ሆነ በፍርሃት መከበር ይገባዋል። እርሱ በፍርድ አያዳላም፤ ጉቦም አይቀበልም። |
አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት፥ መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ” አላቸው።
“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
አይችም ተነሣሁ፤ ታላላቆቹንና ሹሞቹንም፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “አትፍሩአቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን አምላካችንን አስቡ፤ ስለ ወንድሞቻችሁም፥ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ስለ ሚስቶቻችሁም፥ ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ” አልኋቸው።
“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኀያል ጽኑዕና የተፈራኸው አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእኛና በነገሥታቶቻችን፥ በአለቆቻችንም፥ በካህናቶቻችንም፥ በነቢያቶቻችንም፥ በአባቶቻችንም፥ በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።
እግዚአብሔር እርሱ አምላካችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፥ እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያውም በጎች ነን።
“አቤቱ፥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል።
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ።
ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕረትን ታደርጋለህ፤ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ።
መጥተውም “መምህር ሆይ! የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሳር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ?” አሉት።
አለቆች የመሰሉት ግን ቀድሞ እነርሱ እንዴት እንደ ነበሩ ልናገር አያገደኝም፤ እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና፤ አለቆች የመሰሉትም ከራሳቸው ምንም ነገር የጨመሩልኝ የለምና።
እናንተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣችሁን እያበረዳችሁ፥ በደላቸውንም ይቅር እያላችሁ፥ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ ፊት አይቶ የማያዳላ ጌታ በእነርሱና በእናንተ ላይ በሰማይ እንደ አለ ታውቃላችሁና።
በፍርድም ፊት አትዩ፤ ለትልቁም፥ ለትንሹም በእውነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታድሉ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ፤
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።
“የመጻተኛውንና የድሃ-አደጉን፥ የመበለቲቱንም ፍርድ አታጣምምባቸው፤ የመበለቲቱንም ልብስ ለመያዣ አትውሰድባት።
ከፊታቸው አትደንግጥ፤ አምላክህ እግዚአብሔር፥ ከአንተ ጋር ነውና፥ እርሱም አምላክህ እግዚአብሔር ታላቅና ጽኑዕ ነውና።
“እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ነው፤ እርሱ ያውቃል። እስራኤልም ያውቀዋል። በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ለበደልና ለመካድ ከሆነ ዛሬ አያድነን፤
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”