La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ዝ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እነ​ሆም፥ እና​ንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ብዙ​ዎች ናችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላካችሁ እግዚአብሔር ቍጥራችሁን ጨምሯል፤ ስለዚህ ዛሬ እናንተ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችኋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ አምላካችሁ አብዝቶአችኋል፥ እነሆም፥ እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዛት ናችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር አምላካችሁ ቊጥራችሁን አብዝቶአል፤ እነሆ፥ አሁን ቊጥራችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዙ ነው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላካችሁ እግዚአብሔር አብዝቶአችኋል፥ እነሆም፥ እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዛት ናችሁ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 1:10
17 Referencias Cruzadas  

ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው።


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝቡ እስ​ራ​ኤ​ልን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ያበዛ ዘንድ ተና​ግሮ ነበ​ርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነ​በ​ሩ​ትን አል​ቈ​ጠ​ረም።


ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


ዘራ​ች​ሁን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የተ​ና​ገ​ር​ኋ​ትን ምድር ሁሉ ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል ብለህ በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ዐስብ።”


ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አብ​ር​ሃም፥ ወደ ወለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ወደ ሳራ ተመ​ል​ከቱ፤ አንድ ብቻ​ውን በሆነ ጊዜ ጠራ​ሁት፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ ወደ​ድ​ሁ​ትም፤ አበ​ዛ​ሁ​ትም።


በእ​ርሻ ላይ እንደ አለ ቡቃያ አበ​ዛ​ሁሽ፤ አን​ቺም አደ​ግሽ፤ ታላ​ቅም ሆንሽ፤ በእ​ጅ​ጉም አጌ​ጥሽ፤ ከከ​ተማ ወደ ከተማ ገባሽ፤ ጡቶ​ች​ሽም አጐ​ጠ​ጐጡ፤ ጠጕ​ር​ሽም አደገ፤ ነገር ግን ዕር​ቃ​ን​ሽን ሆንሽ፤ ተራ​ቍ​ተ​ሽም ነበ​ርሽ።


የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።


ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም በተ​ጓዙ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደመና ቀን ቀን በላ​ያ​ቸው ላይ ነበረ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ቍጥር ላይ እልፍ አእ​ላ​ፋት ይጨ​ምር፤ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁም ይባ​ር​ካ​ችሁ።


አባ​ቶ​ችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዛ​ት​ህን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አደ​ረገ።


በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ከብ​ዛ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት የነ​በ​ረው ቍጥ​ራ​ችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀ​ራል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የመ​ረ​ጣ​ችሁ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ስለ በዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ እና​ንት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ጥቂ​ቶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤