ቈላስይስ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በመብልም ቢሆን፥ በመጠጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን፥ በመባቻም ቢሆን፥ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ በምትበሉትም ሆነ በምትጠጡት ወይም በዓልን፣ ወር መባቻንና ሰንበትን በማክበር ነገር ማንም አይፍረድባችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ፥ በዓላትን ወይም የወር መባቻን፥ ወይም ሰንበትን በማክበር ምክንያት ማንም አይፍረድባችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፤ |
በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየበዓላቱም እንደ ሥርዐቱ ቍጥር በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ ለማቅረብ፥
በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በበዓላትም ለሚቀርበው ለሚቃጠለው መሥዋዕት ንጉሡ ከገንዘቡ የሚከፍለውን ወሰነ።
የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ኅብስተ ገጽም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቍርባንና ስለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኀጢአት መሥዋዕት፥
ሕቴርሰታ ነህምያም፥ ጸሓፊውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡንም የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ነው፤ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።
ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጐልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤ አቤቱ፥ አምላኬ፥ በመሰንቆ አመሰግንሃለሁ።
መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
እኔም፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ይህ አግባብ አይደለም፤ እነሆ ሰውነቴ አልረከሰችም፤ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥንብና አውሬ የሰበረውን ከቶ አልበላሁም፤ ርኵስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም” አልሁ።
በየበዓላቱም፥ በየመባቻውም፥ በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን መስጠት በአለቃው ላይ ይሆናል፤ እርሱ ለእስራኤል ቤት ያስተሰርይ ዘንድ የኀጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርባል።”
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥
ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ በወርም መባቻ፥ በሚቃጠልም መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ንፉ፤ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።”
ነገር ግን ለጣዖት ከሚሠዋው፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደም ከመብላት እንዲርቁ፥ ለራሳቸው የሚጠሉትንም በወንድሞቻቸው ላይ እንዳያደርጉ እዘዙአቸው።
እንግዲህ በወንድምህ ላይ የምትፈርድ አንተ ምንድን ነህ? ወንድምህንስ የምትነቅፍ አንተ ምንድን ነህ? ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለንና።
ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።
እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥምቀትም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።
ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም።
ዳዊትም ዮናታንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ ።