እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳይነድ ለአምላካችሁ ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
ቈላስይስ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀጢአትን ሰውነት ሸለፈት በመግፈፍ በክርስቶስ መገረዝ በሰው እጅ የአልተደረገ መገረዝን በእርሱ ሆናችሁ ተገረዛችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱ ሆናችሁ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ ተገረዛችሁ፤ በክርስቶስም መገረዝ የሥጋን ኀጢአታዊ ባሕርይ አስወገዳችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ መገረዝ የሥጋዊውን አካል በመግፈፍ በሰው እጅ ባልተከናወነ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱም በማመናችሁ ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ ኃጢአተኛውን የሥጋ ባሕርይ ለማስወገድ በክርስቶስ የተደረገ ነው እንጂ በሰው እጅ የተደረገ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ፤ |
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳይነድ ለአምላካችሁ ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
ስምንት ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት፤ በማኅፀንዋ ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለትም ስሙን ኢየሱስ አሉት።
ዳሩ ግን አይሁዳዊነት በስውር ነው፤ መገዘርም በመንፈስ የልብ መገዘር እንጂ በኦሪት ሥርዐት አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ነገር ግን የኀጢአትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለው አሮጌው ሰውነታችን እንደ ሆነ ይህን እናውቃለን፤ ከእንግዲህ ወዲያ ዳግመና ለኀጢአት እንገዛ ዘንድ አንመለስም።
በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም፥ በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን።
ከክርስቶስ ጋርም ተሰቀልሁ፤ ሕይወቴም አለቀች፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሕይወት አለሁ፤ ዛሬም በሥጋዬ የምኖረውን ኑሮ የወደደኝን ስለ እኔም ራሱን አሳልፎ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እኖራለሁ።
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
ግዙራንስ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናገለግለውና የምናመልከው እኛ ነን፤ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስ እንመካለን እንጂ በሥጋችን የምንመካ አይደለም።
ክርስቶስ ግን ለምትመጣይቱ መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ የሰው እጅ ወደ አልሠራት፥ በዚህ ዓለም ወደ አልሆነችው፥ ከፊተኛዪቱ ወደምትበልጠውና ወደምትሻለው ድንኳን፥
ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ፥ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።