ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
አሞጽ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችግረኛውን በጥዋት የምታስጨንቁ፥ የሀገሩንም ድሃ የምትቀሙ እናንተ ሆይ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ችግረኞችን የምትረግጡ፣ የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ችግረኛውን የምትረግጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ ይህን ስሙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የችግረኞችን መብት የምትረግጡና ድኾችን ከአገር ለማጥፋት የምትፈልጉ ሁሉ! ይህን ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ችጋረኛውን የምትውጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ እናንተ ሆይ፦ |
ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።
ነቢዩም ኤርምያስ ሐሰተኛውን ሐናንያን፥ “ሐናንያ ሆይ ስማ፤ እግዚአብሔር አልላከህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።
በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ መማለጃን ተቀበሉ፤ በአንቺም አራጣና ትርፍ ወስደዋል፤ ቀማኛነትሽንና ኀጢአትሽን ፈጸምሽ፤ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኀጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ ዐውቃለሁና።
አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ የያዕቆብንም ቤት አትዘብዝባቸው ብለሃል።
የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።
እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።