እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።”
ሐዋርያት ሥራ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከታናናሾቹም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ “ታላቁ የእግዚአብሔር ኀይል ይህ ነው” እያሉ ሁሉም ያደምጡት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከታናሽ እስከ ታላቅ ያለው ሰው ሁሉ፣ “ይህ ሰው ‘ታላቁ ኀይል’ በመባል የሚታወቀው መለኮታዊ ኀይል ነው” በማለት ከልብ ያዳምጡት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ “ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው፤” እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሁሉ ትንሹም ትልቁም “ይህ ሰው ታላቅ ተብሎ የሚጠራው የእግዚአብሔር ኀይል ነው!” እያሉ በጥንቃቄ ያዳምጡት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ፦ “ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው” እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር። |
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።”
የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የሐናንያ ልጅ ኢዛንያስ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ መጡ።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋልና፥ ከሐሳዊ ነቢይ ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰትን አደረጉ።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
እነርሱ ግን ወዲያውኑ የሚያብጥ ወይም ሞቶ የሚወድቅ መስሎአቸው ነበር። እያዩትም ብዙ ሰዓት ቆሙ፤ አንዳችም እንደ አልጐዳው በአዩ ጊዜም፥ “ይህስ አምላክ ነው” ብለው ቃላቸውን ለወጡ።
ለእኛ ለዳንነው ግን ከአይሁድ፥ ከአረሚም ብንሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው።
እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን።