Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮናስ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የነ​ነዌ ሰዎ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታ​ላ​ቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፤ ሰዎቹም ሁሉ ከትልቁ እስከ ትንሹ ማቅ ለበሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር አመኑ፤ ጾምም አወጁ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የነነዌ ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል አመኑ፤ ጾምም ዐወጁ፤ መጸጸታቸውንም ለመግለጥ ከታላላቅ ጀምሮ እስከ ታናናሽ ድረስ ሁሉም ማቅ ለበሱ።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 3:5
21 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገባ።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ፈራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሊፈ​ልግ ፊቱን አቀና፤ በይ​ሁ​ዳም ሁሉ ጾም አወጀ።


በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኮ​ሬብ ተራራ ጀም​ረው ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጌጦ​ቻ​ቸ​ውን አወጡ።


እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በደ​ላ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ስ​ብ​ምና።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኢዮ​አ​ቄም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ጾም ዐዋጅ ነገሩ።


የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ኢዛ​ን​ያስ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ መጡ።


የቃ​ር​ሔ​ም​ንም ልጅ ዮሐ​ና​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ፥ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ጠራ፤


ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።


ዐዋ​ጅም አስ​ነ​ገረ፤ በነ​ነ​ዌም ውስጥ የን​ጉ​ሡ​ንና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን ትእ​ዛዝ አሳ​ወጀ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶች፥ ላሞ​ችና በጎች አን​ዳች አይ​ቅ​መሱ፤ አይ​ሰ​ማ​ሩም፤ ውኃ​ንም አይ​ጠጡ፤


የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።


የነ​ነዌ ሰዎች በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥ​ተው ይፋ​ረ​ዱ​አ​ታል፤ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም፤ ዮናስ በሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ጊዜ ንስሓ ገብ​ተ​ዋ​ልና፤ እነሆ፥ ከዮ​ናስ የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እንደ ነገ​ረኝ እን​ደ​ሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ና​ለ​ሁና።


ከታ​ና​ና​ሾ​ቹም ጀምሮ እስከ ታላ​ላ​ቆቹ ድረስ “ታላቁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ይህ ነው” እያሉ ሁሉም ያደ​ም​ጡት ነበር።


እም​ነ​ትስ ተስፋ ስለ​ም​ና​ደ​ር​ገው ነገር የም​ታ​ረ​ጋ​ግጥ፥ የማ​ና​የ​ው​ንም ነገር የም​ታ​ስ​ረዳ ናት።


ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos