ዳዊትም ሊገናኛቸው ወጥቶ፥ “በሰላም ወደ እኔ መጥታችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእናንተ ጋር አንድ ይሆናል፤ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ መጥታችሁ እንደ ሆነ ግን፥ በእጄ ዓመፅ የለብኝምና የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፥ ይፍረደውም፤” አላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 5:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ ክዳችሁ በዕንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን አስነሣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በዕንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን፣ የአባቶቻችን አምላክ ከሙታን አስነሣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአባቶቻችን አምላክ እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን ከሞት አስነሣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤ |
ዳዊትም ሊገናኛቸው ወጥቶ፥ “በሰላም ወደ እኔ መጥታችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእናንተ ጋር አንድ ይሆናል፤ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ መጥታችሁ እንደ ሆነ ግን፥ በእጄ ዓመፅ የለብኝምና የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፥ ይፍረደውም፤” አላቸው።
አቤቱ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ ይህን አሳብ በሕዝብህ ልብ ላይ ለዘለዓለም ጠብቅ፤ ልባቸውንም ወደ አንተ አቅና።
ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ እንዳለ ኢየሱስን አስነሥቶ ተስፋውን ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል።
እንዲህም አለኝ፤ ‘የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን ታውቅና ጽድቁንም ታይ ዘንድ፥ ቃሉንም ከአንደበቱ ትሰማ ዘንድ መረጠህ።
እግዚአብሔርም አስቀድሞ ልጁን አስነሣላችሁ፤ ሁላችሁም ከክፋታችሁ እንድትመለሱ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”
እኛንስ ክርስቶስ ስለ እኛ የኦሪትን መርገም በመሸከሙ ከኦሪት መርገም ዋጅቶናል፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”