ሐዋርያት ሥራ 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊልክስ ግን አይሁድ ከጥንት ጀምሮ የክርስቲያንን ወገኖች ሕግና ትምህርት እንደሚቃወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለዚህም “እንኪያስ የሺ አለቃው ሉስዮስ በመጣ ጊዜ ነገራችሁን እናውቅ ዘንድ እንመረምራለን” ብሎ ቀጠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊልክስ ግን የጌታን መንገድ በሚገባ ዐውቆ ስለ ነበር፣ “የጦር አዛዡ ሉስያስ ሲመጣ ለጕዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ ነገሩን በቀጠሮ አሳደረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፤” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊልክስ ግን ስለ ክርስትና እምነት በደንብ ያውቅ ስለ ነበር “የጦር አዛዡ ሉስዮስ በመጣ ጊዜ፥ ስለ ጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ አሰናበታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና፦ የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው። |
ዛሬም በደል ሳይኖር በአመጣችሁብን ክርክር እኛ እንቸገራለንና ስለዚህ ክርክር የምንወቃቀሰው ነገር የለም፥” ይህንም ብሎ ሸንጎውን ፈታ።
ሀገረ ገዢውም እንዲናገር ጳውሎስን ጠቀሰው፤ ጳውሎስም እንዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስተዳዳሪ እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ጠባያቸውንም ታውቃለህ። አሁንም ደስ እያለኝ ክርክሬን አቀርባለሁ።
ነገር ግን ይህን አረጋግጥልሃለሁ፤ እኔ በሕግ ያለውን፥ በነቢያትም የተጻፈውን ሁሉ አምኜ እነርሱ ክህደት ብለው በሚጠሩት ትምህርት የአባቶችን አምላክ አመልከዋለሁ።
ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ ከአይሁዳዊት ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ። ልኮም ጳውሎስን አስጠራው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ማመንም የሚናገረውን ነገር ሰማው።
ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የምጽፈው የታወቀ ነገር የለኝም። ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን አገኝ ዘንድ ወደ እናንተ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመጣሁት።
ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች የሥልጣን ደብዳቤ ከሊቀ ካህናቱ ለመነ።