Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 24:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አገረ ገዥውም እንዲናገር በእጁ ምልክት በሰጠው ጊዜ፣ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ ፈራጅ መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ የመከላከያ መልሴን የማቀርበው በደስታ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ገዢውም በጠቀሰው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከብዙ ዘመን ጀምረህ ለዚህ ሕዝብ አንተ ፈራጅ እንደሆንህ አውቃለሁና ደስ እያለኝ ስለ እኔ ነገር እመልሳለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አገረ ገዥው ፊልክስ በእጁ ጠቅሶ ጳውሎስ እንዲናገር ፈቀደለት፤ ጳውሎስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለብዙ ዓመቶች የዚህ አገር ገዢ መሆንክን ስለማውቅ ለቀረበብኝ ክስ መከላከያዬን በአንተ ፊት ሳቀርብ በጣም ደስ እያለኝ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ገዡም በጠቀሰው ጊዜ ጳውሎስ መለሰ እንዲህ ሲል፦ ከብዙ ዘመን ጀምረህ ለዚህ ሕዝብ አንተ ፈራጅ እንደ ሆንህ አውቃለሁና ደስ እያለኝ ስለ እኔ ነገር እመልሳለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 24:10
12 Referencias Cruzadas  

ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።


አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “ስለ ራስህ ትና​ገር ዘንድ ፈቅ​ደ​ን​ል​ሃል” አለው፤ ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎስ እጁን አነ​ሣና ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦


አህ​ያም አም​ጥ​ተው ጳው​ሎ​ስን በዚያ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ቂሣ​ርያ አገረ ገዢ ወደ ፊል​ክስ እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘ​ዛ​ቸው።


በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።


በዚያ የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም እስ​ክ​ን​ድ​ሮስ የሚ​ባል አይ​ሁ​ዳዊ ሰውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ነሡ፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ በእጁ ምል​ክት ሰጠና ለሕ​ዝቡ ሊከ​ራ​ከ​ር​ላ​ቸው ወደደ።


ስለ ትም​ህ​ር​ትና ስለ ስሞች፥ ስለ ሕጋ​ች​ሁም የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ዕወቁ፤ እኔ እን​ዲህ ያለ ነገር ልሰማ አል​ፈ​ቅ​ድም።”


ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ ዝም እን​ዲሉ አዘ​ዘና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ ሁሉ፥ ስሙ።


እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በአ​ን​ዲት ከተማ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ፈራ፥ ሰው​ንም የማ​ያ​ፍር አንድ ዳኛ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።


ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።


ወደ አደ​ባ​ባይ ወደ ሹሞ​ቹና ወደ ነገ​ሥ​ታቱ፥ ወደ መኳ​ን​ን​ቱም በሚ​ወ​ስ​ዱ​አ​ችሁ ጊዜ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን አታ​ስቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios