Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፤” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ፊልክስ ግን የጌታን መንገድ በሚገባ ዐውቆ ስለ ነበር፣ “የጦር አዛዡ ሉስያስ ሲመጣ ለጕዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ ነገሩን በቀጠሮ አሳደረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ፊልክስ ግን ስለ ክርስትና እምነት በደንብ ያውቅ ስለ ነበር “የጦር አዛዡ ሉስዮስ በመጣ ጊዜ፥ ስለ ጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ አሰናበታቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ፊል​ክስ ግን አይ​ሁድ ከጥ​ንት ጀምሮ የክ​ር​ስ​ቲ​ያ​ንን ወገ​ኖች ሕግና ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ቃ​ወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም “እን​ኪ​ያስ የሺ አለ​ቃው ሉስ​ዮስ በመጣ ጊዜ ነገ​ራ​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ እን​መ​ረ​ም​ራ​ለን” ብሎ ቀጠ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና፦ የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 24:22
11 Referencias Cruzadas  

ስለ እርሱም ወደ ጌታዬ የምጽፈው እርግጥ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን ነገር አገኝ ዘንድ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ!በፊትህ አመጣሁት፤


ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ አይሁዳዊት ከነበረች ድሩሲላ ከሚሉአት ከሚስቱ ጋር መጥቶ ጳውሎስን አስመጣ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ማመን የሚናገረውን ሰማው።


ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤


ገዢውም በጠቀሰው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከብዙ ዘመን ጀምረህ ለዚህ ሕዝብ አንተ ፈራጅ እንደሆንህ አውቃለሁና ደስ እያለኝ ስለ እኔ ነገር እመልሳለሁ፤


መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፤ እንደ ሕጋችንም እንፈርድበት ዘንድ ወደድን።


እነርሱም ብዙ ጊዜ እንዲቀመጥላቸው ሲለምኑት እሺ አላለም፤


ፈራጆችም ጉዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፤ ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ የሐሰት ክስ አቅርቦ ከተገኘ፥


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ ተረዳ።


በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።


ዛሬ ስለተደረገው ‘ሁከት ነው፤’ ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፤ ምክንያት የለምና።” ይህንም ብሎ ጉባኤውን ፈታው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios