La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከጳ​ው​ሎ​ስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕ​ይ​ወት ሊኖር አይ​ገ​ባ​ው​ምና እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ከም​ድር አስ​ወ​ግ​ደው” እያሉ ጮሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቡም ይህን ቃል እስኪናገር ድረስ ሰሙት፤ ከዚህ በኋላ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፣ “ይህስ ከምድር ገጽ ይወገድ! በሕይወት መኖር አይገባውም!” ብለው ጮኹበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፥ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና አሉ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 22:22
6 Referencias Cruzadas  

ሁሉም በሙሉ፥ “ይህን አስ​ወ​ግ​ደው፥ ስቀ​ለ​ውም፥ በር​ባ​ንን ግን ፍታ​ልን” ብለው ጮሁ።


እነ​ርሱ ግን፥ “አስ​ወ​ግ​ደው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ። ጲላ​ጦ​ስም፥ “ንጉ​ሣ​ች​ሁን ልስ​ቀ​ለ​ውን?” አላ​ቸው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱም፥ “ከቄ​ሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለ​ንም” ብለው መለሱ።


ብዙ​ዎ​ችም ይከ​ተ​ሉት ነበር፤ ሕዝ​ቡም፥ “አስ​ወ​ግ​ዱት” እያሉ ይጮሁ ነበር።


ፊስ​ጦ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ እና​ን​ተም ከእኛ ጋር ያላ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ችሁ፥ ስሙ፤ አይ​ሁድ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እን​ዳ​ይ​ገ​ባው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆነ በዚህ እየ​ጮሁ የለ​መ​ኑኝ ይህ የም​ታ​ዩት ሰው እነሆ።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።