ሐዋርያት ሥራ 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህም አድርገው በበርናባስና በሳውል እጅ ወደ ቀሳውስት ላኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርዳታውንም በበርናባስና በሳውል እጅ ለሽማግሌዎቹ በመላክ፣ ይህንኑ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ደግሞ አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ላኩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መዋጮም አድርገው በበርናባስና በሳውል እጅ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት። |
በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም አስከትለውት መጡ።
ሕዝቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳውሎስንና በርናባስንም ተከራከሩአቸው፤ ስለዚህ ነገርም ጳውሎስንና በርናባስን፥ ጓደኞቻቸውንም በኢየሩሳሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሊልኳቸው ተማከሩ።
እንዲህ የምትል መልእክትም በእጃቸው ጻፉ፤ “ከሐዋርያትና ከቀሳውስት ከወንድሞችም በአንጾኪያ፥ በሶርያና በኪልቅያ ለሚኖሩ፥ ከአሕዛብ ላመኑ ወንድሞቻችን ትድረስ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ ደስ ይበላችሁ።
ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም ምእመናንና ሐዋርያት፥ ቀሳውስትም ተቀበሉአቸው፤ እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ያደረገላቸውን ነገሩአቸው።
በሐዋርያትም ዘንድ ትርጓሜዉ የመጽናናት ልጅ የሚሆን በርናባስ የተባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚሉት አንድ የቆጵሮስ ሰው ነበር።
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤