Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከመ​ሊ​ጡም የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ቀሳ​ው​ስት ይጠ​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ኤፌ​ሶን ላከ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተ ክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጳውሎስ ከሚሊጢ ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን አስጠራ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 20:17
15 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።


በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።


ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።


በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤


በየ​ከ​ተ​ማ​ውም ሲሔዱ፥ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያዘ​ዙ​ትን ሥር​ዐት አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው።


እን​ዲህ የም​ትል መል​እ​ክ​ትም በእ​ጃ​ቸው ጻፉ፤ “ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትና ከቀ​ሳ​ው​ስት ከወ​ን​ድ​ሞ​ችም በአ​ን​ጾ​ኪያ፥ በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅያ ለሚ​ኖሩ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ትድ​ረስ፤ ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስ​ትም ስለ​ዚህ ነገር የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ያዩ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው።


ወደ ኤፌ​ሶ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም ተዋ​ቸ​ውና እርሱ ብቻ​ውን ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ አይ​ሁ​ድን ተከ​ራ​ከ​ራ​ቸው።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ከዚያ ወጥ​ተን በኪ​ዮስ ፊት ለፊት ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሳሞስ አለ​ፍን፤ በት​ሮ​ጊ​ሊ​ዮም ተቀ​መ​ጥን፤ ከዚህ ቀን በኋ​ላም ወደ መሊጡ ደረ​ስን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios