በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
2 ሳሙኤል 15:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አልወድድህም ቢለኝ፥ እነሆኝ በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን ያድርግብኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እርሱ፣ ‘ባንተ አልተደሰትሁም’ የሚል ከሆነ፣ መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግብኝ፤ እኔም ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እርሱ፥ ‘ባንተ አልተደሰትሁም’ የሚል ከሆነ፥ እነሆኝ፥ መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግብኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ባላገኝ ግን በእኔ ላይ የወደደውን ያድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፦ አልወድድህም ቢለኝ፥ እነሆኝ፥ ደስ የሚያሰኘውን ያድርግብኝ አለው። |
በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
የልቅሶዋም ወራት ሲፈጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስትም ሆነችው፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆነ።
የአባቴ ቤት ሁሉ በጌታዬ በንጉሥ ዘንድ ሞት የሚገባቸው ነበሩ፤ አንተ ግን እኔን ባሪያህን በገበታህ በሚበሉ መካከል አስቀመጥኸኝ፤ ለንጉሥ ደግሞ ለመናገር ምን መብት አለኝ?”
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደህ አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤ አምላክህ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናቸው ዘንድ ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድንና ጽድቅን ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች።
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፥ “እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፤ ዛሬ ግን እባክህ አድነን” አሉት።
ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፤ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።