ኤልያስም፥ “እግዚአብሔርን ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስራኤልን አልገለባብጥም።
2 ጴጥሮስ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዐመፃን ደመወዝ ወደደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀናውን መንገድ ትተው፣ የዐመፅን ደመወዝ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ስተዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዓመፃን ደመወዝ ወደደ፥ |
ኤልያስም፥ “እግዚአብሔርን ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስራኤልን አልገለባብጥም።
ኤልያስም፥ “ሁሉን ለሚገዛ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና፤ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ” አለ።
የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ አልተቀበሉአቸውምና፥ ይረግማቸውም ዘንድ በለዓምን ገዝተውባቸዋልና፤ ነገር ግን አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት መለሰው።
ተመልሰውም ከጥላው ሥር ይቀመጣሉ፤ በሕይወትም ይኖራሉ፤ ከእህሉም የተነሣ ይጠግባሉ፤ እንደ ወይንም አረግ ያብባሉ ፤ መታሰቢያውም እንደ ሊባኖስ ወይን ይሆናል።
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።
እርሱም በአህያዪቱ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ሁለቱም ብላቴናዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ። አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመንገዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ ይመልሳት ዘንድ አህያዪቱን መታት።
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ቀና አልነበረምና ላሰናክልህ ወጥቼአለሁ፤
እነርሱ በበለዓም ምክር በፌጎር ምክንያት የእስራኤልን ልጆች የሚያስቱ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል እንዲስቱ የሚያደርጉ ዕንቅፋቶች ናቸውና፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆኖአል፤
ከዚህም በኋላ ይህ ሰው በዐመፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በምድር ላይም በግንባሩ ወደቀና ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።
እንዲህም አለው፥ “ሽንገላንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ፥ የሰይጣን ልጅ፥ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ ማጣመምህን ትተው ዘንድ እንቢ አልህን?
የዐመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤
ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።
ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አሳያችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይንና እግዚአብሔርን ማገልገልን በመተው እርሱን እበድል ዘንድ እግዚአብሔር ይህን አያድርግብኝ።