2 ነገሥት 9:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመልሰውም ለኢዩ ነገሩት፤ እርሱም፥ “በባሪያው በቴስብያዊው ኤልያስ እጅ በኢይዝራኤል እርሻ የኤልዛቤልን ሥጋ ውሾች ይበላሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመልሰውም ይህን ሲነግሩት፣ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለባሪያው ለቴስብያዊው ለኤልያስ፣ በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበሉታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ሁሉ ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “ይህ ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ ቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‘የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ሁሉ ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “ይህ ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ ቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‘የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሰውም ነገሩት፤ እርሱም “በባሪያው በቴስብያዊ ኤልያስ ‘በኢይዝራኤል እርሻ የኤልዛቤልን ሥጋ ውሾች ይበላሉ፤ |
የሶርያም ንጉሥ አገልጋዮች እንዲህ አሉት፥ “የእስራኤል አምላክ የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም፤ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ብንዋጋቸው ድል እናደርጋቸው ነበር።
በጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ አፍ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሔማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።
ለኢዩ፥ “ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ” ተብሎ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እንዲሁም ሆነ።