የእኩሌቶቹ ፈረሶች አለቃ ዘምሪም አሽከሮቹን ሁሉ ሰብስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በመጋቢው በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።
2 ነገሥት 9:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይንዋን ተኳለች፤ ራስዋንም አስጌጠች፤ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይኗን ተኳኵላ፣ ጠጕሯንም አሰማምራ በመስኮት ትመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጒርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቊልቊል መንገዱን ትመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል መጣ፤ ኤልዛቤልም በሰማች ጊዜ ዐይንዋን ተኳለች፤ ራስዋንም አስጌጠች፤ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር። |
የእኩሌቶቹ ፈረሶች አለቃ ዘምሪም አሽከሮቹን ሁሉ ሰብስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በመጋቢው በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።
የሶርያም ንጉሥ አገልጋዮች እንዲህ አሉት፥ “የእስራኤል አምላክ የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም፤ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፤ ነገር ግን በሜዳ ብንዋጋቸው ድል እናደርጋቸው ነበር።
አንቺስ ምን ታደርጊያለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዐይንሽንም በኵል በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፤ ፍቅረኞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
ከሩቅ ሀገርም ወደመጡ ሰዎች መልእክተኞችን ላኩ፤ እነርሱም በደረሱ ጊዜ ይታጠባሉ፤ ዐይኖቻቸውንም ይኳላሉ፤ ያጌጣሉም።
በቀስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙታንን ልቅሶ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈሮችህንም አትሸፍን፤ የዕዝን እንጀራንም አትብላ።”
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።