Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 9:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይኗን ተኳኵላ፣ ጠጕሯንም አሰማምራ በመስኮት ትመለከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጒርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቊልቊል መንገዱን ትመለከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ኢዩም ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ፤ ኤል​ዛ​ቤ​ልም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ዐይ​ን​ዋን ተኳ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም አስ​ጌ​ጠች፤ በመ​ስ​ኮ​ትም ዘልቃ ትመ​ለ​ከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል መጣ፤ ኤልዛቤልም በሰማች ጊዜ ዐይንዋን ተኳለች፤ ራስዋንም አስጌጠች፤ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 9:30
12 Referencias Cruzadas  

ከሹማምቱ አንዱና የግማሽ ሠረገሎቹ አዛዥ የሆነው ዘምሪ ዐምፆ ተነሣበት፤ በዚያ ጊዜ ኤላ በቴርሳ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፤


“ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር፣ ‘በኢይዝራኤል ቅጥር አጠገብ ውሾች ኤልዛቤልን ይበሏታል’ ይላል።


ውበቷን በልብህ አትመኝ፤ በዐይኗም አትጠመድ።


ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።


አንቺ ለጥፋት የተዳረግሽ ሆይ፤ ምን መሆንሽ ነው? ቀይ ቀሚስ የለበስሽው ለምንድን ነው? ለምን በወርቅ አጌጥሽ? ዐይኖችሽንስ ለምን ተኳልሽ? እንዲያው በከንቱ ተሽሞንሙነሻል፤ የተወዳጀሻቸው ንቀውሻልና፤ ነፍስሽንም ሊያጠፉ ይፈልጋሉ።


“ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው።


ድምፅህን ዝቅ አድርገህ በሐዘን አንጐራጕር እንጂ ለሞተው አታልቅስ። ጥምጥምህን ከራስህ አታውርድ፤ ጫማህንም አታውልቅ፤ አፍህ ድረስ አትሸፋፈን፤ የዕዝን እንጀራም አትብላ።”


ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤


ፍልስጥኤማውያን ሰራዊታቸውን ሁሉ በአፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ሸለቆ ባለው ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos