አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
2 ነገሥት 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰላይም ያያቸው ዘንድ በኢይዝራኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመጡም የእነኢዩን አቧራ አየ። “እነሆም፥ አቧራ አያለሁ” አለ። ኢዮራምም፥ “ይገናኛቸው ዘንድ አንድ ፈረሰኛ ይሂድ፤ እርሱም፦ ሰላም ነውን? ይበላቸው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢይዝራኤል ግንብ ማማ ላይ የቆመው ጠባቂ የኢዩ ወታደሮች መቅረባቸውን አይቶ፣ “ኧረ ወታደሮች መጡ” በማለት ጮኾ ተናገረ። ኢዮራምም፣ “አንድ ፈረሰኛ ተጠርቶ፤ እንዲገናኛቸው ላኩትና፣ ‘የመጣችሁት በሰላም ነውን?’ ብሎ ይጠይቅ” ሲል አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢይዝራኤል ከተማ መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ቃፊር ኢዩና ተከታዩ ጭፍራ ሲመጡ መቃረባቸውን አይቶ፥ “ሰዎች እየጋለቡ ሲመጡ አያለሁ!” ሲል የጥሪ ድምፅ አሰማ። ኢዮራምም “አንድ ፈረሰኛ ልከህ የሚመጡትን ሰዎች ሰላም ነውን? ብሎ እንዲጠይቅ አድርግ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢይዝራኤል ከተማ መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ቃፊር ኢዩና ተከታዩ ጭፍራ ሲመጡ መቃረባቸውን አይቶ፥ “ሰዎች እየጋለቡ ሲመጡ አያለሁ!” ሲል የጥሪ ድምፅ አሰማ። ኢዮራምም “አንድ ፈረሰኛ ልከህ የሚመጡትን ሰዎች ሰላም ነውን? ብሎ እንዲጠይቅ አድርግ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢይዝራኤልም ግንብ ላይ የቆመው ሰላይ የኢዩ ጭፍራ ሲመጣ አይቶ “ጭፍራ አያለሁ፤” አለ። ኢዮራምም “የሚገናኘው ፈረሰኛ ላክ፤ እርሱም ‘ሰላም ነውን?’ ይበለው፤” አለ። |
አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ወጣ፤ ዐይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ።
እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።
ኢዩም ወደ ጌታው ብላቴኖች ወጣ፤ እነርሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እርሱም፥ “ሰውዬው ፌዝ እንደሚናገር አታውቁምን?” አላቸው።
የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ አረማውያን የሶርያ ሰዎች በሬማት ያቈሰሉትን ቍስል በኢይዝራኤል ይታከም ስለ ነበረ ኢዩ በሰረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ። ጠንካራና ኀይለኛ ሰው ነበርና፤ የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ኢዮራምን ለማየት ወርዶ ነበር።
ፈረሰኛውም ሊቀበላቸው ሄዶ፥ “ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ሰላም ነውን?” አላቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመልሰህ ተከተለኝ” አለ። ሰላዩም፥ “መልእክተኛው ደረሰባቸው፥ ነገር ግን አልተመለሰም” ብሎ ነገረው።
ሁለተኛውንም ፈረሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነርሱም ደርሶ ንጉሡ እንዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመልሰህ ተከተለኝ” አለ።
ሁሉም ዕውራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ በመኝታቸውም ሕልምን ያልማሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጠባቂዎችሽን በቅጥርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁሜአለሁ፤ እግዚአብሔርን የሚያስቡ ከቶ ዝም አይሉም፤
ሳሙኤልም እግዚአብሔር የተናገረውን አደረገ፤ ወደ ቤተ ልሔምም መጣ። የከተማውም ሽማግሌዎች በተገናኙት ጊዜ ደነገጡ፥ “ነቢይ! የመጣኸው ለሰላም ነውን?” አሉት።