ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፤ በዐይኖቹም የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፤ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።
2 ነገሥት 6:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢዩም፣ “ከእኛ ጋራ ያሉት ከእነርሱ ጋራ ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “አይዞህ አትፍራ፤ ከእነርሱ ጋር ከተሰለፈው ይልቅ ከእኛ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት ይበልጣል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “አይዞህ አትፍራ፤ ከእነርሱ ጋር ከተሰለፈው ይልቅ ከእኛ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት ይበልጣል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ፤” አለው። |
ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፤ በዐይኖቹም የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፤ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።
የኤልሳዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነሥቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማዪቱ ዙሪያ ጭፍሮች ከተማዋን ከብበዋት አየ። ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናድርግ?” አለው።
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ከኃጥኣን ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤ ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላምን ከሚናገሩ ዐመፅ አድራጊዎች ጋር አትጣለኝ።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው።