በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ።
2 ነገሥት 25:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዓምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬዎች ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባቢሎናውያን የናስ ዐምዶቹን፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የነበሩትን ተንቀሳቃሽ የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ከናስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ሰባበሩ፤ ናሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዐምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬ ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ። |
በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ።
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።
በቤቱም ፊት ቁመታቸው ሠላሳ አምስት ክንድ የነበረውን ሁለቱን ዐምዶች ሠራ፤ በእያንዳንዳቸውም ላይ የነበረው ጕልላት አምስት ክንድ ነበረ።
የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንም ቤት መዝገብ፥ የአለቆቹንም ቤት መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
ለመሠዊያው ክዳን ሥራለት፤ መሸፈኛውን፥ ጽዋዎቹን፥ የሥጋ ሜንጦዎቹን፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም አድርግ። ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ።
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አያስቀሩልህም፤ ይላል እግዚአብሔር።
የዚችንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪቷንም ሁሉ፥ ክብርዋንም ሁሉ፥ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ይበዘብዙአቸዋል፤ ይዘውም ወደ ባቢሎን ያስገቡአቸዋል።
ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።