በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪያል ኢያሪኮን ሠራ፤ በነዌም ልጅ በኢያሱ ቃል እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ በበኵር ልጁ በአቢሮን መሠረቷን አደረገ፥ በታናሹ ልጁም በዜጉብ በሮችዋን አቆመ።
2 ነገሥት 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፥ “እነሆ፥ ጌታችን እንደምታይ የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው፤ ውኃው ግን ክፉ ነው፤ ሴቶችም ሲጠጡት ይመክናሉ፥” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው “ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው “ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማይቱም ሰዎች ኤልሳዕን “እነሆ፥ ጌታችን እንደምታይ የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው፤ ውሃው ግን ክፉ ነው፤ ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች፤” አሉት። |
በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪያል ኢያሪኮን ሠራ፤ በነዌም ልጅ በኢያሱ ቃል እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ በበኵር ልጁ በአቢሮን መሠረቷን አደረገ፥ በታናሹ ልጁም በዜጉብ በሮችዋን አቆመ።
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ፥ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ፥ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸውን፥ ይህን ያደረግሁትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አልሰማህምን?
አብድዩም በመንገድ ብቻውን ሳለ እነሆ፥ ኤልያስ ሊገናኘው ብቻውን መጣ፤ አብድዩም ሮጠና፥ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኤልያስ አንተ ነህን?” አለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ውሰድ፤ በግብፅ ውኆች፥ በወንዞቻቸው፥ በመስኖዎቻቸውም፥ በኩሬዎቻቸውም፥ በውኃ ማከማቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆናል፤” በግብፅም ሀገር ሁሉ በዕንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።
አምላክህ እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ከብቶችህን በማብዛት እግዚአብሔር በጎነቱን ያበዛልሃል።
ከተማዪቱም በእርስዋም ያለው ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እርም ይሆናሉ፤ የላክናቸውን መልእክተኞች ስለ ሸሸገች ዘማዊቱ ረዓብ፥ ከእርስዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕይወት ይኖራሉ።
በዚያችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረቷን በበኵር ልጁ የሚጥል፥ በሮችዋንም በታናሹ ልጁ የሚያቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።