በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
2 ነገሥት 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ አካዝም የአሦርን ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶርን ሊገናኘው ወደ ደማስቆ ሄደ፤ በደማስቆ የነበረውንም መሠዊያ አየ፤ ንጉሡም አካዝ የመሠዊያውን ምሳሌና የአሠራሩን መልክ ወደ ካህኑ ወደ ኦርያ ላከው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሥ አካዝ የአሦርን ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶርን ለመገናኘት ወደ ደማስቆ ሄደ። በደማስቆም ያለውን መሠዊያ አይቶ፣ ንድፉን ከዝርዝር ጥናቱ ጋራ ለካህኑ ለኦርያ ላከለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ አካዝ ወደ ደማስቆ ሄዶ ከንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ጋር በተገናኘ ጊዜ በዚያ አንድ መሠዊያ አየ፤ ያንን መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኡሪያ ላከለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አካዝ ወደ ደማስቆ ሄዶ ከንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ጋር በተገናኘ ጊዜ በዚያ አንድ መሠዊያ አየ፤ ያንን መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኡሪያ ላከለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ አካዝም የአሦርን ንጉሠ ቴልጌልቴልፌልሶርን ሊገናኘው ወደ ደማስቆ ሄደ፤ በደማስቆ የነበረውን መሠዊያ አየ፤ ንጉሡም አካዝ የመሠዊያውን ምሳሌና የአሠራሩን መልክ ወደ ካህኑ ወደ ኦርያ ላከው። |
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ካህኑም ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ እንደ ላከለት መሠዊያውን ሁሉ ሠራ፤ እንዲሁም ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ እስኪመጣ ድረስ ሠራው።
ዕውቀት እንደ ተሰጠው የእግዚአብሔርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈውን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለዳም ተነሣ፤ ከተራራውም በታች መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለትም ድንጋዮችን ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አቆመ።
ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።
የታመኑትን ሰዎች ካህኑን ኦርያንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ምስክሮች አድርግልኝ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮባቸዋልና፤”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፤ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና።
እነርሱም ስለ ሠሩት ሥራ ሁሉ መቅሠፍታቸውን ያገኛሉ፤ አንተም የቤቱን መልክና ምሳሌውን፥ መውጫውንም፥ መግቢያውንም፥ ሥርዐቱንም፥ ሕጉንም ሁሉ አስታውቃቸው፤ ሥርዐቱንና ሕጉን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ፥ ያደርጉትም ዘንድ በፊታቸው ጻፈው።
መድረካቸውን በመድረኬ አጠገብ፥ መቃናቸውንም በመቃኔ አጠገብ አድርገዋልና። በእኔና በእነርሱ መካከል ግንብ ብቻ ነበረ፤ በሠሩትም ርኵሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ፤ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።
በጣዖቶቻቸውም ፊት አገልግለዋቸው ነበሩና፥ ለእስራኤልም ቤት የኀጢአት እንቅፋት ሆነዋልና ስለዚህ እጄን በላያቸው አንሥቻለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ይሸከማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ልባችሁንም አድሱ፤ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን፥ ፍጹሙንም መርምሩ።
አምላኮቻቸውንም እንዳትሻ፥ አሕዛብም ለአምላኮቻቸው እንደሚያደርጉ እኔም አደርጋለሁ እንዳትል ራስህን ጠብቅ።
ኋላ ይህ በተደረገ ጊዜ ነገ ለእኛ ወይም ለትውልዳችን ይህን ሲሉ፥ እኛ፦ እነሆ፥ አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ቍርባን አይደለም እንላለን።
ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።