ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ተባለች። ከተማዋንም ዙሪያዋን እስከ ዳርቻዋ ድረስ ቀጠራት፤ ቤቱንም ሠራ።
2 ነገሥት 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮቹም የኢያሙሃት ልጅ ኢያዜክርና የሳሜር ልጅ ኢያዛብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ ልጁም አሜስያስ በፋንታው ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፥ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፤ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት። |
ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ተባለች። ከተማዋንም ዙሪያዋን እስከ ዳርቻዋ ድረስ ቀጠራት፤ ቤቱንም ሠራ።
ከበለዓን ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐመፀበት፤ ናባጥና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤልም ሀገር ባለው በገባቶን ገደለው።
በነጋውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝቡንም ሁሉ፥ “እናንተ ንጹሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌታዬን ቤት የወነጀልሁ የገደልኋቸውም እኔ ነኝ፤ እነዚህንስ ሁሉ የገደለ ማን ነው?
በይሁዳ ንጉሥ በአካዝያስ ልጅ በኢዮአስ በሃያ ሦስተኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ በሰማርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመትም ነገሠ።
እንዲሁም የናሜሲ ልጅ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮራምን ከዳው። ኢዮራምና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል የተነሣ ሬማት ዘገለዓድን ይጠብቁ ነበር።
የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ያን ባየ ጊዜ በአትክልት ቤት መንገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እርሱንም ደግሞ አልተወውም” ብሎ ተከተለው። በይብላሄምም አቅራቢያ ባለችው በጋይ አቀበት በሰረገላው ላይ ወጋው። ወደ መጊዶም ሸሸ፥ በዚያም ሞተ።
ከእርሱም ዘንድ አልፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪያዎቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮአዳ ልጅ ደም ተበቅለው በአልጋው ላይ ገደሉት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ነገር ግን በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።