Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከበ​ለ​ዓን ቤት የሆነ የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ ዐመ​ፀ​በት፤ ናባ​ጥና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ገባ​ቶ​ንን ከብ​በው ነበ​ርና ባኦስ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ልም ሀገር ባለው በገ​ባ​ቶን ገደ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ናዳብና መላው እስራኤል በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከብበው ሳሉ፣ ከይሳኮር ነገድ የተወለደው የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐምፆ በመነሣት ናዳብን በገባቶን ገደለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባዕሻ በናዳብ ላይ ዐምፆ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባዕሻ በናዳብ ላይ ዐምፆ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ከይሳኮርም ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ተማማለበት፤ ናዳብና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤም አገር ባለው በገባቶን ገደለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 15:27
15 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ቤት የሚ​ያ​ጠፋ ንጉሥ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያነ​ግ​ሣል፤ እር​ሱም ዛሬ ይደ​ረ​ጋል፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ምን እና​ገ​ራ​ለሁ?


ከዳ​ንም ነገድ ኤል​ቆ​ታ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ገባ​ቶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


አል​ቃታ፥ ቤጌ​ቶን፥ ጌቤ​ላን፥


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት ዘምሪ በቴ​ርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ግን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር በገ​ባ​ቶን ሰፍ​ረው ነበር።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።


ዘን​በ​ሪም ከእ​ርሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከገ​ባ​ቶን ወጥ​ተው ቴር​ሳን ከበቡ። በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጡ።


የእ​ኩ​ሌ​ቶቹ ፈረ​ሶች አለቃ ዘም​ሪም አሽ​ከ​ሮ​ቹን ሁሉ ሰብ​ስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴ​ርሳ ነበረ፤ በቴ​ር​ሳም በነ​በ​ረው በመ​ጋ​ቢው በአሳ ቤት ይሰ​ክር ነበር።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአሳ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ባኦስ ናባ​ጥን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ።


በእ​ጁም ሥራ ያስ​ቈ​ጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስላ​ደ​ረ​ገው ክፋት ሁሉ እር​ሱ​ንም ስለ ገደ​ለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በባ​ኦ​ስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢዩ መጣ።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት ዘምሪ ገብቶ ወጋና ገደ​ለው፤ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ።


በሰ​ፈር ያሉ ሕዝ​ቡም “ዘምሪ ከድቶ ኤላን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ” ሲሉ ሰሙ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዚያ ቀን በሰ​ፈሩ ውስጥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ዘን​በ​ሪን አነ​ገሡ።


እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios