ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
2 ነገሥት 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበሩት፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሱ፤ ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም ለእግዚአብሔር ቤት ጠባቂዎችን ሾመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የአገሩ ሕዝብ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የበዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደለው። ዮዳሄ ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደለው። ዮዳሄ ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑም ለእግዚአብሔር ቤት አስተዳዳሪዎችን ሾመ። |
ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
ኢዩም ወደ እስራኤል ሀገሮች ሁሉ ላከ፤ የበዓልም አገልጋዮች ሁሉ፥ ካህናቱም ሁሉ፥ ነቢያቶቹም ሁሉ መጡ፤ ከእነርሱም ሳይመጣ የቀረ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም። ሁሉም ወደ በዓል ቤት ገቡ፤ የበዓልንም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞሉት።
የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አቅርበው በፈጸሙ ጊዜ ኢዩ ዘበኞቹንና አለቆቹን፥ “ግቡና ግደሉአቸው፤ አንድም አያምልጥ” አላቸው። በሰይፍም ስለት ገደሉአቸው፤ ዘበኞችና አለቆችም ወደ ውጭ ጣሉአቸው፤ ወደ በዓልም ቤት ከተማ ሄዱ።
በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፤ ሐውልቶችንም ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ነቃቀለ፤ የእስራኤል ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙንም “ነሑስታን” ብሎ ጠራው።
ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዲሠዋ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነበረውን ጣፌትን ርኩስ አደረገው።
በዚያም የነበሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ካህናት ሁሉ በመሠዊያዎቹ ላይ ገደላቸው፥ የሰዎቹንም አጥንት በመሠዊያዎቹ ላይ አቃጠለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
ወደ ይሁዳም ወጡ፤ በረቱባቸውም፤ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም፥ ሴቶች ልጆቹንም ወሰዱ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አልቀረለትም።
የበዓሊምንም መሠዊያዎች በፊቱ አፈረሰ፤ በላዩም የነበሩትን ኮረብታዎችን ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የተቀረጹትንና ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች ሰባበረ፤ አደቀቃቸውም፤ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብርም ላይ በተናቸው።
መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎችም አደቀቀ፤ በእስራኤልም ሀገር ሁሉ የኮረብታዎችን መስገጃዎችአጠፋ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ ፈጨው፤ አደቀቀውም፤ በውኃም ላይ በተነው፤ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣቸው።
እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩባቸውን፥ በረዥም ተራሮች፥ በኮረብቶችም ላይ ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉት፤
መሠዊያቸውንም አፍርሱ፤ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐጸዶቻቸውንም ቁረጡ፤ የአማልክቶቻቸውንም ምስሎች በእሳት አቃጥሉ፤ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ።
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና በድንጋይ ይውገሩት፤ ይግደሉትም።
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥