2 ነገሥት 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የበዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደለው። ዮዳሄ ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚያም የአገሩ ሕዝብ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደለው። ዮዳሄ ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበሩት፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሱ፤ ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም ለእግዚአብሔር ቤት ጠባቂዎችን ሾመ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑም ለእግዚአብሔር ቤት አስተዳዳሪዎችን ሾመ። Ver Capítulo |