ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
2 ነገሥት 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአካዝያስም እናት ጎቶልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነሥታ የመንግሥትን ዘር ሁሉ አጠፋች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ፣ ንጉሣውያን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጇን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአካዝያስም እናት ጎቶልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነሥታ የመንግሥትን ዘር ሁሉ አጠፋች። |
ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
ንጉሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአባቴ በዳዊት ላይ የሠራኸውን፥ ልብህም ያሰበውን ክፋት ሁሉ ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም ክፋትህን በራስህ ላይ ይመልሳል።
ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የሀገሩ ሰዎች የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው ገደሉአቸው፤ ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።
ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሳቢያ የተባለች የቤርሳቤህ ሴት ነበረች።
በሰባተኛው ወር ግን የመንግሥት ዘር የነበረ የኤልሴማ ልጅ የናታንዩ ልጅ እስማኤል መጣ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶልያንም መታው፤ ሞተም፤ ከእርሱም ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንንም ገደላቸው።
መንገሥም በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች።
የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ያን ባየ ጊዜ በአትክልት ቤት መንገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እርሱንም ደግሞ አልተወውም” ብሎ ተከተለው። በይብላሄምም አቅራቢያ ባለችው በጋይ አቀበት በሰረገላው ላይ ወጋው። ወደ መጊዶም ሸሸ፥ በዚያም ሞተ።
ጎቶልያ ከሐዲት ነበረችና ልጆችዋም የእግዚአብሔርን ቤት አፍርሰዋልና፤ በእግዚአብሔርም ቤት ተቀድሶ የነበረውን ሁሉ ለበኣሊም ሰጥተዋልና።
እንዲህም ሆነ፤ በሰባተኛው ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ መሴፋ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በመሴፋ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ።
እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ” አለው።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ወደ አባቱም ቤት ወደ ኤፍራታ ገባ፤ ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው፤ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ።