2 ነገሥት 10:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበዓልን ሐውልት ቀጠቀጡ፤ የበዓልንም ቤት አፈረሱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የውዳቂ መጣያ አደረጉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበኣልን ማምለኪያ ምስል ቀጠቀጡ፤ የበኣልንም ቤተ አምልኮ አፈረሱ፤ ይህንም ሕዝቡ እስከ ዛሬ ድረስ የኵስ መጣያው አድርጎታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ዓይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዓይነት ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዐይነት ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበኣልን ሐውልት ቀጠቀጡ፤ የበኣልንም ቤት አፈረሱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የውዳቂ መጣያ አደረጉት። |
የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበሩት፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሱ፤ ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም ለእግዚአብሔር ቤት ጠባቂዎችን ሾመ።
በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፤ ሐውልቶችንም ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ነቃቀለ፤ የእስራኤል ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙንም “ነሑስታን” ብሎ ጠራው።
በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ ነገር ግን እንደ አባቱና እንደ እናቱ አልነበረም፤ አባቱም ያሠራውን የበዓልን ምስል አጠፋ።
ይህንም ትእዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ምሰሶው ከቤቱ ተነቅሎ እርሱ ይሰቀልበት፤ በላዩም ይገደል፤ ቤቱም የጕድፍ መጣያ ይደረግ ብዬ አዝዣለሁ።
ነገር ግን መሠውያዎቻቸውን ታፈርሳላችሁ፤ ሐውልቶቻቸውንም ትሰብራላችሁ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውን ትቈርጣላችሁ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት ታቃጥላላችሁ፤
የኮረብታ መስገጃዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በእጅ የተሠሩ የዕንጨት ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፤ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ ከእነርሱም የተሠራባቸውን ብርንና ወርቅን፥ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትበድልበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፤ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ምስል በእሳት አቃጥሉ።