La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም የም​ለው በእ​ና​ንተ ለመ​ፍ​ረድ አይ​ደ​ለም፤ ለሞ​ትም፥ ለሕ​ይ​ወ​ትም ቢሆን እና​ንተ በል​ባ​ችን እን​ዳ​ላ​ችሁ ፈጽሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን የምለው ልኰንናችሁ አይደለም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ፣ በልባችን ውስጥ ስፍራ አላችሁ፤ ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም ዐብረን ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህን የምለው እናንተን ለመኮነን አይደለም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን ስፍራ እንዳላችሁ አስቀድሜ ተናግሬለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም የምለው በእናንተ ላይ ለመፍረድ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደ ነገርኳችሁ እናንተ በልባችን ውስጥ ናችሁ፤ ስለዚህ በሕይወትም ሆነ በሞት ሁልጊዜ ከእናንተ አንለይም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለኵነኔ አልልም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን እንዳላችሁ አስቀድሜ ብዬአለሁና።

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 7:3
12 Referencias Cruzadas  

ስለ​ምን ነው? አል​ወ​ዳ​ች​ሁ​ምና ነውን? እን​ደ​ም​ወ​ድ​ዳ​ች​ሁስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።


የእ​ኛስ መጽ​ሐ​ፋ​ችን እና​ንተ ናችሁ፤ በል​ባ​ችን ውስ​ጥም ተጽ​ፋ​ች​ኋል፤ ትታ​ወ​ቃ​ላ​ች​ሁም፤ ሰውም ሁሉ ያነ​ብ​ባ​ች​ኋል።


ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋ​ችሁ ይታ​ወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደ​ለና ስለ ተበ​ደለ ሰው አይ​ደ​ለም።


ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና።


እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፤ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና።