Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኀይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኃይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 13:10
11 Referencias Cruzadas  

እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።


የእኔ ደስታ የሁ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ በሁ​ላ​ችሁ አም​ኛ​ለ​ሁና በመ​ጣሁ ጊዜ ደስ ሊያ​ሰ​ኙኝ ከሚ​ገ​ባ​ቸው ኀዘን እን​ዳ​ያ​ገ​ኘኝ ይህን ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።


ለዕ​ው​ነት ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን እንጂ፤ ከዕ​ው​ነት መው​ጣት አን​ች​ል​ምና።


ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እሠ​ራ​ለሁ፤ በሥ​ጋዊ ሥር​ዐ​ትም እን​ደ​ም​ን​ኖር አድ​ር​ገው በሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩን ሰዎች ላይ በድ​ፍ​ረት ለመ​ና​ገር አስ​ባ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን በዚህ ዓይ​ነት ድፍ​ረት እን​ድ​ና​ገር እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጉኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ።


እን​ዴት ሆኜ ወደ እና​ንተ ልመጣ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ? በበ​ትር ነውን? ወይስ በፍ​ቅ​ርና በቅ​ን​ነት መን​ፈስ?


ጥን​ቱን አስ​ቀ​ድሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም አስ​ቀ​ድሜ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ቀድሞ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገ​ር​ሁ​አ​ችሁ፥ አስ​ቀ​ድሞ ለበ​ደሉ፥ ለሌ​ሎ​ችም ሁሉ እንደ ገና የመ​ጣሁ እንደ ሆነ ርኅ​ራኄ እን​ዳ​ላ​ደ​ርግ፥ እን​ዲሁ ሳል​ኖር ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ እና​ገ​ራ​ለሁ፥


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ፥ በእኔ ሥል​ጣን፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ኀይል፥


በን​ጽ​ሕ​ናና በዕ​ው​ቀት፥ በም​ክ​ርና በመ​ታ​ገሥ፥ በቸ​ር​ነ​ትና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ አድ​ልዎ በሌ​ለ​በት ፍቅር፥


የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios