2 ቆሮንቶስ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለሆን ራሳችንን እናንጻ፤ ሥጋችንን አናርክስ፤ ነፍሳችንንም አናሳድፍ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት የምንቀደስበትን እንሥራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፤ ይህ የተስፋ ቃል ስላለን፣ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ፥ ይህ ሁሉ ተስፋ የተሰጠው ለእኛ ስለ ሆነ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችን ፍጹም እንዲሆን እናድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። |
ክፉ ሰው መንገዱን፥ በደለኛም ዐሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ፤ እርሱም ይምረዋል፤ እርሱ ብዙ በደላችሁን ይተውላችኋልና።
አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የዝሙትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም ላይ አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?
ልብሱ ወይም ድሩ ወይም ማጉ ወይም ከቆዳ የተደረገው ነገር ከታጠበ በኋላ ደዌው ቢለቅቀው ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።
እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ሁሉ በክርስቶስ እውነት ሆኖአልና፤ ስለዚህም በእርሱ ለእግዚአብሔር ክብር አሜን እንላለን።
እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን።
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥
ስለዚህ የማይናወጥ መንግሥትን ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሀት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ።
እንግዲህ አንፍራ፤ ወደ ዕረፍቱም እንድንገባ ትእዛዙን አንተው፤ ከእናንተም ምንአልባት በተለመደ ስሕተት የሚገኝና የሚጸና ቢኖር ወደ ዕረፍቱ እንዲገባ የሚተዉት አይምሰለው።
የተመረጣችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምንም እንኳን እንዲህ ብንላችሁ ሕይወት ወዳለባት ትምህርት እንድትቀርቡ እንታመንባችኋለን።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችሁማል፤ ያበረታችሁማል።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።