Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፤ ይላል ሁሉን የሚችል ጌታ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ለእናንተም አባት እሆናለሁ፤ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፤” ይላል ሁሉንም የሚገዛ ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እኔ አባታችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፥ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 6:18
21 Referencias Cruzadas  

ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።


ለተ​ቀ​በ​ሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚ​ያ​ምኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ዲ​ሆኑ ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው።


እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጅ ይሆ​ነ​ኛል፤ ክፉ ነገ​ርም ቢያ​ደ​ርግ፥ በሰ​ዎች በት​ርና በሰው ልጆች አለ​ንጋ እገ​ሥ​ጸ​ዋ​ለሁ፤


ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ “አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፤” ይላል።


ልጁ በብ​ዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች መካ​ከል በኵር ይሆን ዘንድ አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ው​ንና የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ልጁን ይመ​ስሉ ዘንድ አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።


እያ​ለ​ቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማ​ጽ​ና​ናት አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በወ​ንዝ ዳር በቅን መን​ገድ አስ​ሄ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም አይ​ሰ​ና​ከ​ሉም፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አባት ነኝና፥ ኤፍ​ሬ​ምም በኵሬ ነውና።”


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ሁላ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሆነ​ና​ልና።


ከዚ​ህም በኋላ አብ​ራም የዘ​ጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው “በፊ​ትህ የሄ​ድሁ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መል​ካም አድ​ርግ፤ ንጹ​ሕም ሁን፤


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ውድ ፈቃዱ ለእ​ርሱ ልጆች ልን​ሆን አስ​ቀ​ድሞ ወሰ​ነን።


ሰሜ​ንን፦ መል​ሰህ አምጣ፤ ደቡ​ብ​ምን፦ አት​ከ​ል​ክል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችን ከሩቅ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ከም​ድር ዳርቻ፥


“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወ​ን​ዶች ልጆች መካ​ከል እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብን የሚ​ገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ውን ምድር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ አባቴ ትለ​ኛ​ለህ፤ ከእ​ኔም አት​መ​ለ​ስም አልሁ ብለ​ሃ​ልና።


በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።


ያዕ​ቆብ ዮሴ​ፍን አለው፥ “አም​ላኬ በከ​ነ​ዓን ምድር በሎዛ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ ባረ​ከ​ኝም።


እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል፤ ከአ​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት እን​ዳ​ራ​ቅሁ፥ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።


የዓ​ለም ተስ​ፋው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ መም​ጣት ይጠ​ባ​በቅ ነበ​ርና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios