2 ቆሮንቶስ 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክርስቶስ ዕውነት አብሮኝ ይኖራልና፥ ይህቺ ደስታዬ በአካይያ አውራጃ አልተከለከለችብኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክርስቶስ እውነት በውስጤ እስካለ ድረስ፣ በአካይያ አውራጃ ይህን ትምክሕቴን ማንም ሊገታው አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክርስቶስ እውነት በእኔ እንዳለ፥ ይህ ትምክህቴ በአካይያም አገር ዝም የሚያሰኘኝ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ በመኖሩ እንዳልመካ የሚያደርገኝ በአካይያ አገሮች ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክርስቶስ እውነት በእኔ እንዳለ፥ ይህ ትምክህት በእኔ ዘንድ በአካይያ አገር አይከለከልም። |
ወደ አካይያም ሊሄድ በወደደ ጊዜ ወንድሞች አጽናኑት፤ እንዲቀበሉትም ወደ ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ ወደ እነርሱም በደረሰ ጊዜ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ ላመኑት ብዙ አስተማራቸው፤ ትልቅ ርዳታም ረዳቸው።
ባለማቋረጥ በምጸልየው ጸሎት እንደማስባችሁ ልጁ በአስተማረው ወንጌል በፍጹም ልቡናዬ የማመልከው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
በቤታቸው ያሉትን ማኅበረ ክርስቲያንም ሰላም በሉ፤ ወዳጄ ኤጴኔጦስንም እንዴት ነህ? በሉ፤ ይኸውም በእስያ በክርስቶስ ላመኑ ሁሉ መጀመሪያቸው ነው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ የእስጢፋኖስና የፈርዶናጥስ፥ የአካይቆስም ቤተሰቦች፥ የአካይያ መጀመሪያዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማልዳችኋለሁ።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ጳውሎስና ከወንድማችን ጢሞቴዎስ በቆሮንቶስ ሀገር ላለችው የእግዚአሔር ቤተ ክርስቲያንና በአካይያ ሀገር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፥
እኛስ በማይገባ ሌላ በደከመበት አንመካም፤ ነገር ግን ሃይማኖታችሁ እንድትሰፋ፥ የተሠራችላችሁ ሕግም በእናንተ እንድትጸና ተስፋ እናደርጋለን።
ነገር ግን ያደረግሁትም ቢሆን፥ የማደርገውም ቢሆን፥ እነርሱ እንደ እኛ የሚመኩበትን ያገኙ ዘንድ፥ ምክንያት የሚሹትን ምክንያት አሳጣቸው ዘንድ ነው።
ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ሐሰት እንደማልናገር ያውቃል።
እኛስ ደግሞ ስለ ራሳችን የምንከራከራችሁ ይመስላችኋልን? በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን፤ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ይህ ሁሉ ግን እናንተ ትታነጹ ዘንድ ነው።
እናንተ እንደምትተጉ አውቃለሁና፤ ስለዚህም “የአካይያ ሰዎች እኮ ከአምና ጀምሮ አዘጋጅተዋል” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ አመሰገንኋችሁ፤ እነሆም የእናንተ መፎካከር ብዙዎችን ሰዎች አትግቶአቸዋል።
ከክርስቶስ ጋርም ተሰቀልሁ፤ ሕይወቴም አለቀች፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሕይወት አለሁ፤ ዛሬም በሥጋዬ የምኖረውን ኑሮ የወደደኝን ስለ እኔም ራሱን አሳልፎ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እኖራለሁ።